ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ሊቨርፑል በቀጣይ ምን ያስፈርማል ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ሊቨርፑል በቀጣይ ምን ያስፈርማል ?
ሊቨርፑል በቀጣይ ምን ያስፈርማል ?

ሊቨርፑል ከሳላህ ጋር በመለያየቱ እንዲሁም ሁጎ ኤኪቲኬ በመጎዳቱ ምክንያት የፊት መስመሩ ሳስቶ ይገኛል።

ሊቨርፑሎች የአለም ሻምፒዮኑን ቪክቶር ሙኖዝ በማስፈረም ቡድኑን አጠናክረዋል።

ይሁን እንጂ ሊቨርፑል ቢያንስ አንድ ሁለገብ የፊት መስመር አጥቂ እንደሚያስፈልገው ይታመናል።

በተጨማሪም ሊቨርፑል የመሐል ሜዳውን እና የቀኝ መስመር ተከላካይ ቦታውን ሊያጠናክር ይችላል።

ሊቨርፑል አሁን ላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ከውድድር አመቱ መጀመር በፊት ሞሀመድ ሳላህን የሚተካ ተጨዋች ማስፈረም መሆኑ ተገልጿል።

የፒኤስጂው ብራድሌይ ባርኮላ ሊቨርፑል ወደ ቡድኑ ሊያካትተው የሚፈልገው ተጨዋች መሆኑን ለክለቡ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ዘግበዋል።

በተጨማሪም ክለቡ ሌሎች አማራጮችን እየተመለከተ እንደሚገኝ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች