ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ መጫወት የማቆመው እናንተ ሳትሆኑ እኔ ስፈልግ ነው ” ሮናልዶ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ መጫወት የማቆመው እናንተ ሳትሆኑ እኔ ስፈልግ ነው ” ሮናልዶ
“ መጫወት የማቆመው እናንተ ሳትሆኑ እኔ ስፈልግ ነው ” ሮናልዶ

“ 23 አመት እኔን ለመጣል ሞክራችኋል


ፖርቹጋላዊው ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከስፔን ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር።

ሮናልዶ በቆይታው “ መጫወት የማቆመው እኔ ስፈልግ ብቻ ነው ጋዜጠኞች ስትፈልጉ አይደለም ” ሲል ተናግሯል።

ጋዜጠኞችን ክፉኛ የተቸው ሮናልዶ “ እኔን ለ 23 አመት ለመጣል ሞክራችኋል ነገርግን ዋጋ ቢስ መሆኑንም ተረድታችኋል ጊዜ ማባከን ነው “ ብሏቸዋል።

አክሎም “ በጣም የሚወዱኝ አሉ ብዙም የማይወዱኝም አሉ የህይወት አካል ነው እኔም ምርጫ አለኝ “ ብሏል።

“ እኔን ከልብ የሚደግፉትን ሁልጊዜ አስባቸዋለሁ ” ያለው ሮናልዶ ለሌሎቹ ግን ግድ አይሰጠኝም ሲል ተደምጧል።

“ ነገ ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረግ አለብን ምርጥ ቀን እንደሚሆን አምናለሁ ጨዋታውን የምናሸንፍ ይሆናል “ ሮናልዶ

ሮናልዶ አያይዞም የመጨረሻው አለም ዋንጫ መሆኑን አስታውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች