ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ማድሪድ ተጨዋች ለማስፈረም ንግግር ጀመረ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ማድሪድ ተጨዋች ለማስፈረም ንግግር ጀመረ !
ማድሪድ ተጨዋች ለማስፈረም ንግግር ጀመረ !

ሪያል ማድሪድ ኮትዲቯራዊውነሰ የሌፕዚግ የክንፍ ተሰላፊ ያን ድዮማንዴ ለማስፈረም ወደ ዝውውሩ መግባቱ ተገልጿል።

ሎስ ብላንኮዎቹ የ 19ዓመቱን የፊት መስመር ተሰላፊ ወደ ስብስባቸው ለመቀላቀል ከሌፕዚግ ጋር ንግግር ጀምረዋል።

ፒኤስጂ ተጫዋቹን የማስፈረም ፍላጎት ሲኖራቸው ተጫዋቹም የመጀመሪያ ምርጫው አድርጎ ነበር።

ይሁን እንጂ ፒኤስጂ ሌፕዚግ ተጫዋቹን ለመሸጥ እንዲያስብ የሚያደርግ ሂሳብ ለማቅረብ ፍቃደኛ አይደለም ተብሏል።

አሁን ላይ ሪያል ማድሪድ ወደ ዝውውሩ መግባቱ የተጫዋቹን ዝውውር ሁኔታ መቀየሩ ተዘግቧል።

ሪያል ማድሪድ ከዚህ በፊት ብራሂም ዲያዝ ምናልባት ክለቡን ከለቀቀ ያን ድዮማንዴን ለማምጣት አቅዶ ነበር።

ይሁን እንጂ ብራሂም ዲያዝ አሁን ላይ በክለቡ መቆየት ቢፈልግም ሪያል ማድሪድ ድዮማንዴን ለማምጣት እንቅስቃሴ ጀምሯል።

መረጃው የ ዘ አትሌቲክ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች