ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ሞሮኮ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ሞሮኮ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች !
ሞሮኮ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች !

በጭማሪ ደቂቃ ጎል አስቆጥራ ወደ መለያያ ምት የደረሰችው ሞሮኮ 3ለ2 በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች።

ኔዘርላንድ በኮዲ ጋክፖ ግብ ስትመራ ብትቆይም ኢሳ ዲዮፕ በ 9️⃣2️⃣ኛ ደቂቃ ላይ ሞሮኮን አቻ ማድረግ ችሎ ነበር።

በመለያያ ምቱ ሁለቱ ሀገራት አምስት የመለያያ ምቶችን ሳይጠቀሙበት ቀርተው ነበር።

አሽራፍ ሀኪሚ እና ኤል አይናዊ በሞሮኮ በኩል እንዲሁም ካላይቨርት ፣ ቲምበር እና ሰምርቪል የኔዘርላንድን መለያያ ምት የሳቱ ተጫዋቾች ናቸው።

ኔዘርላንድ በአለም ዋንጫው ከውድድሩ ውጪ የሆነች ሌላኛው የአውሮፓ ሀገር ሆናለች።

ሞሮኮ በቀጣይ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከአምስት ቀናት በኃላ ከአዘጋጇ ካናዳ ጋር የምትጫወት ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች