ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ሲቲ ላይ ትልቁ ቅጣት መጣል አለበት ” ዣቪየር ቴባስ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ሲቲ ላይ ትልቁ ቅጣት መጣል አለበት ” ዣቪየር ቴባስ
“ ሲቲ ላይ ትልቁ ቅጣት መጣል አለበት ” ዣቪየር ቴባስ

የስፔን ላሊጋው ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ማንችስተር ሲቲ ላይ ትልቅ ቅጣት እንዲጣል ጠየቁ።

ዣቪየር ቴባስ ሲናገሩም “ በፕሪሚየር ሊጉ ያለው ትልቅ የቅጣት ህግ መተግበር አለበት ” ሲሉ ገልፀዋል።

“ የማንችስተር ሲቲ ቅጣት ለወደፊት መማሪያነት ማገልገል አለበት ” ያሉት ፕሬዝዳንቱ “ ከአስር አመት በላይ ህግ መጣስ ከባድ ነገር ነው “ ብለዋል።

ፕሪሚየር ሊጉ ማንችስተር ሲቲ ላይ ያቀረባቸውን የፋይናንስ ደንብ ጥሰት ክሶች ይፋ አድርጓል።

ከእነዚህ ውስጥ :-

- እስከ 830 ሚልዮን የሚሆን ገንዘብ ማጭበርበር

- ሀሰተኛ ስፖንሰርሺፕ ስምምነት መፈረም

- ለዘጠኝ አመታት የቀጠለ ማጭበርበር

- የፋይናንስ መረጃዎችን ይፋ አለማድረግ

- ከምርመራው ጋር አልተባበርም ማለት እንደሚገኝበት ተገልጿል።

ተዛማጅ ታሪኮች