ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ስፔን እንግሊዝን አሸንፋለች !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ስፔን እንግሊዝን አሸንፋለች !
ስፔን እንግሊዝን አሸንፋለች !

በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ስፔን እንግሊዝን ዌምብሌይ ስታዲየም ላይ ገጥማ 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።

ላሚን ያማል ፣ ኦያርዛባል እና ቤና የስፔንን የአሸናፊነት ግቦች አስቆጥረዋል።

ለሶስቱ አናብስት ግቦችን ሀሪ ኬን እና አንቶኒ ጎርደን ከመረብ አሳርፈዋል።

ሚኬል ኦያርዛባል ለስፔን ብሔራዊ ቡድን ባደረጋቸው 15 ጨዋታዎች 14 ግብ አስቆጥሯል።

በጨዋታው ሀሪ ኬን ፍፁም ቅጣት ምት መጠቀም ሳይችል ቀርቷል።

ላሚን ያማል እንግሊዝ ላይ የተቆጠረ በታሪክ ሶስተኛውን ፈጣን ጎል ( 2' ) አስቆጥሯል።

በዚህ ምድብ የምትገኘው ክሮሽያ በበኩሏ ቼክ ሪፐብሊክን 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች።

የ 41ዓመቱ አማካይ ሉካ ሞድሪች በጨዋታው ለክሮሽያ አንድ ግብ አስቆጥሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች