ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ በአርጀንቲና እና ግብፅ ጨዋታ ትክክለኛ ዳኝነት ነበር ” ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ በአርጀንቲና እና ግብፅ ጨዋታ ትክክለኛ ዳኝነት ነበር ” ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ
“ በአርጀንቲና እና ግብፅ ጨዋታ ትክክለኛ ዳኝነት ነበር ” ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ

“ ሜሲ ገና ወጣት ይመስላል ”


የስፔን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ የግብፅ እና አርጀንቲናን ጨዋታ የመሩትን ዳኛ አድንቀዋል።

“ በጨዋታው ስለነበረው ዳኝነት የተነሳውን ክርክር መረዳት አልቻልኩም ከየት እንደመጣ አላውቅም ” ሲሉ ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ ተናግረዋል።

“ ጨዋታውን ተመልክቻለሁ ” ያሉት አሰልጣኙ “ ዳኛው በሁሉም ውሳኔዎች ጥሩ ነበር ያደረገው ሁሉ ትክክል ስለነበረ እንኳን ደስ አለህ ልለው እፈልጋለሁ ” ብለዋል።

ስለ ሜሲ ያነሱት አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ
ሜሲ በአሁኑ ሰዓት የተለየ ብቃቱን እያሳየ ነው ፤
በሀያ አመቱ የነበረውን ይመስላል “ ሲሉ ተደምጠዋል።

አክለውም “ እሱ ባሳካው ነገር የማይረካ እና የማይደክም ተጨዋች ነው በየቀኑ የበለጠ ማድረግ ይፈልጋል ለሁሉም የቡድን አጋሮቹ አርአያ ነው ” ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች