ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

በፍፃሜው ከስፔን ምን እንጠብቅ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
በፍፃሜው ከስፔን ምን እንጠብቅ ?
በፍፃሜው ከስፔን ምን እንጠብቅ ?

የስፔን ብሔራዊ ቡድኑ ኳስ በመቆጣጠር እና ስኬታማ አጭር ቅብብሎችን እያደረገ ይጫወታል።

ስፔን ይህን የታወቀችበት አጨዋወት በውድድሩ ስታስመለክት በሰባቱ ጨዋታዎች አማካይ የኳስ ቁጥጥሯ 63.7% ነበር።

ስፔን ኳስ ተቆጣጥራ መጫወቷ ተቃራኒ ቡድን በአካል እና በአዕምሮ እንዲዳከም ያደርጋል።

የቡድኑ አቀራረብ ኳስ ተቆጣጥሮ ተጋጣሚውን በማድከም ክፍተት መጠበቅን ያለመ ብቻ አይደለም።

የስፔን ተጨዋቾች ቦታቸውን እየቀያየሩ ለተመልካች ሳቢ የጨዋታ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ይስተዋላሉ።

እንዲሁም ወደፊት ፈጣን ሩጫዎችን በማድረግ እና የተጋጣሚ ተከላካዮችን ቅርፅ በማሳጣት ክፍተት ለማግኘት ይጫወታሉ።

በዛሬው ጨዋታም በስፔን በኩል ኳስ የሚቆጣጠር ፣ የተደራጀ እና ከኳስ ውጪ ጠንክሮ የሚከላከል ቡድን ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች