ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ባሎን ዶር ካሸነፍኩ መታሰቢያነቱን ለአፍሪካ አበረክታለሁ ” ኪሊያን ምባፔ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ባሎን ዶር ካሸነፍኩ መታሰቢያነቱን ለአፍሪካ አበረክታለሁ ” ኪሊያን ምባፔ
“ ባሎን ዶር ካሸነፍኩ መታሰቢያነቱን ለአፍሪካ አበረክታለሁ ” ኪሊያን ምባፔ

ፈረንሳዊው ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ባሎን ዶር ካሸነፈ መታሰቢያነቱን ለአፍሪካ እንደሚያደርግ ገልጿል።

የካሜሮን የዘረ ሀረግ ያለው ምባፔ " ፈረንሳይ ብወለድም አስተዳደጌ በአፍሪካ ባህል የተቃኘ ነው "ሲል ገልጿል።

“ ወደ አፍሪካ ስሄድ ህዝቡ ከፍተኛ አቀባበል ያደርግልኛል ከህዝቡ ፍቅር ይሰማኛል “ ሲል ጨምሮ ተናግሯል።

ለአፍሪካ የባሎን ዶር ድምፅ ሰጪዎች መልዕክት ያስተላለፈው ምባፔ “ በመጀመሪያ እስካሁን ለሰጡኝ ድጋፍ አመሰግናለሁ "ብሏል።

አክሎም " አፍሪካን ለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ እግሬ እዛ በሄደ ቁጥር የመወደድ ስሜት ይሰማኛል " ብሏል።

ከአፍሪካ የተገኘ እንደመሆኑ ሰዎች ከባሎን ዶር ጋር ስሙን ሲጠሩ እንደሚደሰት ኪሊያን ምባፔ ተናግሯል።

“ የባሎን ዶር ሽልማቱን አሸንፌ መታሰቢያነቱን ለአፍሪካ እንደማደርግ ተስፋ አደርጋለሁ ” ኪሊያን ምባፔ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች