ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ብራዚል ኖርዌይን አሸንፋ አታውቅም ” ሶልባከን

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ብራዚል ኖርዌይን አሸንፋ አታውቅም ” ሶልባከን
“ ብራዚል ኖርዌይን አሸንፋ አታውቅም ” ሶልባከን

“ ብራዚል እንደ ድሮ አይደለችም ”

የኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሶልባከን ኖርዌይ ከብራዚል ጋር የተሻለ ታሪክ እንዳላት ገልጸዋል።

“ ከብራዚል ጋር ብዙ ጨዋታ አላደረግንም ነገርግን በታሪክ ብራዚል ኖርዌይን አሸንፋ አታውቅም ” ሲሉ አሰልጣኝ ሶልባከን ተናግረዋል።

አክለውም “ ብራዚል እና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲን መግጠም ለእኛ ትልቅ ክብር ነው " ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።

ስለጨዋታው ያነሱት አሰልጣኙ “ ብራዚል የማሸነፍ እድሏ በጣም ትልቅ አይደለም እንደ ቀደሞ አይደሉም ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ ቡድኑ ጥሩ ውጤት እያገኘ ነው አጨዋወታችን ያግዘናል 100% ከሆንን ብራዚልን ማሸነፍ እንችላለን ካልሆነ እድል አይኖረንም ” ሶልባከን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች