ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ብዙዎች ይሰናበታሉ ብለው ቢጠብቁም ባለን አቅም እናምናለን ”

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ብዙዎች ይሰናበታሉ ብለው ቢጠብቁም ባለን አቅም እናምናለን ”
“ ብዙዎች ይሰናበታሉ ብለው ቢጠብቁም ባለን አቅም እናምናለን ”

የቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሩዲ ጋርሺያ በቡድናቸው እንደሚተማመኑ ገልጸዋል።

“ የምንገጥመው የዋንጫ አሸናፊነት ቅድመ ግምት ከተሰጠው ቡድን ጋር መሆኑን እናውቃለን ” ሲሉ ሩዲ ጋርሺያ ተናግረዋል።

ስፔን ጠንካራ መሆኗን ያነሱት አሰልጣኙ “ ኳስ ይቆጣጠራሉ የኋላ መስመራቸው ጥብቅ ነው ምንም ጎል አላስተናገዱም " ብለዋል።

አክለውም “ ነገርግን ቁጥሮች ይሰበራሉ ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ግብ ለማስቆጠር እና ለማለፍ እንጫወታለን " ሲሉ ገልፀዋል።

“ ጠንካራ ቡድን አለን ” የሚሉት አሰልጣኙ “ በውድድሩ በማጥቃት ጥሩ ከሆኑ ቡድኖች ሁለተኛው እኛ ነን ብዙም ሞክረናል ብለዋል።

“ ብዙዎች ስንብታችንን ቢጠብቁም ባለን አቅም እናምናለን ለማለፍ ያለንን ሁሉ እንሰጣለን ” ሩዲ ጋርሺያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች