ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ አሁን የድሮዋ ብራዚል የለችም ” ኬንቶ ሽዮጋይ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ አሁን የድሮዋ ብራዚል የለችም ” ኬንቶ ሽዮጋይ
“ አሁን የድሮዋ ብራዚል የለችም ” ኬንቶ ሽዮጋይ

“ ንግግራቸው የበለጠ ያነሳሳናል ” ማርኪንሆስ


የጃፓን ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ኬንቶ ሽዮጋይ ብራዚል አሁን ላይ ጠንካራ አይደለችም በማለት ተናግሯል።

“ ብራዚል በቀደመው ጊዜ ጠንካራ ነበረች ” ያለው ሽዮጋይ “ ግን አሁንስ ? ስለ እነሱ ብዙ አልሰማም “ ብሏል።

ፈረንሳይን የወቅቱ ጠንካራ ሀገር በማለት ሲጠቅስ አርጀንቲናም ጥሩ ቡድን ነች ብሏል።

ስለ ኔይማር ያነሳው ኬንቶ ሽዮጋይ “ ኔይማር ከዚህ የነበረው አቋሙ አሁን የለም ይመስለኛል አሁን ስጋት የለብንም “ ብሏል።

ምላሽ የሰጠዉ ማርኪንሆስ “ ማውራታቸውን መቀጠላቸው ለቡድናችን ለማነሳሳት ይረዳል "ብሏል።

“ እዚህ አሜሪካ ለአንድ ወር ቆይተናል ድምፃችንን አጥፍተን አላማችን ላይ እየሰራን ነው እንደዚህ አይነት ወሬዎችን ለተጋጣሚ እንተዋለን “ ሲል ማርኪንሆስ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች