ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

አራውሆ የኋላ መስመሩን ያሻሽል ይሆን ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
አራውሆ የኋላ መስመሩን ያሻሽል ይሆን ?
አራውሆ የኋላ መስመሩን ያሻሽል ይሆን ?

አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ ከመጨረሻ ጨዋታቸው የአንድ ተጨዋች ለውጥ አድርገው ወደ ሜዳ ይገባሉ።

በዛሬው ጨዋታ ፍሪምፖንግ ተቀያሪ ወንበር ላይ ሲቀመጥ በቀኝ መስመር ቦታ ሮናልድ አራውሆ ተሰልፏል።

አንዶኒ ኢራኦላ ፍሪምፖንግን አስቀምጠው አራውሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በቋሚነት ማሰለፋቸው ትኩረት የሳበ ውሳኔ ሆኗል።

አሰልጣኙ ጠንካራ መሆን ለሚሻው የቡድኑ ተከላካይ ክፍል መፍትሔ ይሆናል ያሉትን ውሳኔ ወስነዋል።

ከባርሴሎና በውሰት የፈረመው አራውሆ የመሐል እና ቀኝ መስመር ተከላካይ ሆኖ ማገልገል ይችላል።

አራውሆ በቀኝ መስመር ቦታው ላይ ምን ሊያስመለክት ይችላል የሚለው ይጠበቃል።

አዲሱ ፈራሚ ብራድሌይ ባርኮላ ከተቀያያሪ ወንበር በመነሳት የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport      @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች