ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

አርሰናል በዝውውሩ ምን እየሰራ ነው ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
አርሰናል በዝውውሩ ምን እየሰራ ነው ?
አርሰናል በዝውውሩ ምን እየሰራ ነው ?

አርሰናል ከቀናት በፊት ብሩኖ ጉማሬሽን ለማስፈረም ለኒውካስል ጥያቄ አቅርቦ ውድቅ ሆኖበታል።

ተጫዋቹን ለማስማማት ችግር የማይሆንባቸው መድፈኞቹ የተሻሻለ ሂሳብ ያቀርቡ እንደሆነ አልታወቀም።

ኒውካስል በበኩሉ ተጨዋቹ አይሸጥም ያለ ሲሆን አርሰናል በቀጥታ እንዳላነጋገራቸው አስረድተዋል።

በሌላ በኩል መድፈኞቹ የፔሮ ሄንካፔን የውሰት ውል ወደ ቋሚነት መቀየራቸውን አረጋግጠዋል።

አርሰናል የመሐል ሜዳው ላይ ትኩረት ቢያደርግም የፊት መስመሩን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑም ተገልጿል።

በተጨማሪም የኋላ መስመር ተሰላፊ ለማስፈረም አማራጮችን እየተመለከቱ እንደሚገኙ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

@tikvahethsport          @YisakAH

ተዛማጅ ታሪኮች