“ አርጀንቲና እንድታሸንፍ የማይፈልጉ ሰዎች አሉ “

“ አርጀንቲና እንድታሸንፍ የማይፈልጉ ሰዎች አሉ “
“ ዘመቻ ተከፍቶብናል “
“ አርጀንቲና ውድድሩን አስደሳች ታደርጋለች “ ሊዮኔል ስካሎኒ
የአለም ሻምፒዮናዋ አርጀንቲና አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ ከዛሬ ምሽቱ ተጠባቂ ጨዋታ በፊት ቡድኑ ላይ ከዳኝነት ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ቅሬታዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
“ ይህ አዲስ ነገር አይደለም ከአርባ አመት በፊት ጀምሮ አርጀንቲና በዳኛ ትታገዛለች ይባላል “ ሲሉ “ እግር ኳስ መረዳት ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ አርጀንቲና ሁሌም ውድድሩን አስደሳች ከሚያደርጉ ሀገራት አንዷ ነች “ ብለዋል።
አሰልጣኙ አክለውም “ ይህን እንደ ማሳያ ለተጫዋቾቼ አርጀንቲና እንድታሸንፍ የማይፈልጉ ሰዎች እንዳሉ ለማሳየት እጠቀምበታለሁ “ ብለዋል።
“ የሚሰጡብን ትችቶች እና አስተያየቶች ከጨዋታ መጀመር በፊት እንደ መነሳሻ ነው የምንጠቀምባቸው “ አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ
ሊዮኔል ስካሎኒ አያይዘው “ ዘመቻ ተከፍቶብናል ፣ የቫር እና ይህ ሁሉ ቴክኖሎጂ እያለን በዳኞች እንታገዛለን መባሉ ከባድ ነው “ ሲሉ ገልፀዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe