ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ አርጀንቲና እንግዳ ነገሮችን እያደረገች ነው ” ላፖርቴ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ አርጀንቲና እንግዳ ነገሮችን እያደረገች ነው ” ላፖርቴ
“ አርጀንቲና እንግዳ ነገሮችን እያደረገች ነው ” ላፖርቴ

“ ውዝግብ ለመፍጠር አትሞክር ” ሰርጂዮ አጉዌሮ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ አይመሪክ ላፖርቴ የአርጀንቲናን የሀይል አጨዋወት ተችቶ ነበር።

ላፖርቴ በሰጠው አስተያየት “ ባለፉት ጨዋታዎች ያልተለመዱ ነገሮች እና የማያስቀጡ ጥፋቶች አይተናል “ ብሏል።

“ በተለይ በአርጀንቲና በኩል ተጨዋቾቻቸው ጠንካራ ጥፋቶችን ሲሰሩ ነበር “ ሲል ላፖርቴ ተችቷል።

“ በእንደዚህ አይነት ውድድር ይህ መፈቀድ የለበትም “ ያለው ተጨዋቹ የሰውን ሀሳብ ወደ ንዴት ይቀይራል " ብሏል።

አክሎም “ ሁኔታው በዳኛው ላይ የተመካ ይሆናል ከቁጥጥር እንዳይወጣ መጠበቅ አለበት " ሲል አሳስቧል።

“ እኛ ጨዋ ቡድን ነን ” የሚለው ላፖርቴ “ ተጋጣሚያችንን በሀይል አናጠቃም ወይም የእብደት ጥፋት አንሰራም "ብሏል።

አርጀንቲናዊው የቀድሞ ተጨዋች ሰርጂዮ አጉዌሮ በበኩሉ “ ምን እያልክ ነዉ ምኑ ነው ያስገረመህ “ ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

“ ስማኝ ውዝግብ ለመፍጠር አትሞክር ምክንያቱም ፊት ለፊት ስንገናኝ ታፈገፍጋለህ ”ሲል ተናግሮታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች