አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ወይስ አርቤሎኣ ?

አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ወይስ አርቤሎኣ ?
ቼልሲ እና ፉልሀም ዛሬ ምሽት በክራቨን ኮቴጅ የፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ጨዋታው ጓደኛሞቹን አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ እና አርቤሎኣ በተቃራኒ የሚያገናኝ በመሆኑ ይበልጥ ተጠባቂ አድርጎታል።
ዣቢ አሎንሶ እና አርቤሎኣ የቀድሞ ጓደኛሞች ሲሆኑ በሊቨርፑል ፣ ሪያል ማድሪድ እና ስፔን በጋራ 262 ጨዋታዎችን አድርገዋል።
ሁለቱ አሰልጣኞች ባለፈው አመት ከሪያል ማድሪድ የተሰናበቱ ሲሆን አሁን ደግሞ ቼልሲ እና ፉልሀምን እየመሩ በተቃራኒ ተገናኝተዋል።
ከአመታት በፊት 2004 ዣቢ አሎንሶ ሊቨርፑልን የተቀላቀሉ ሲሆን አርቤሎኣ ደግሞ 2007 ወደ ሊቨርፑል ሄደዋል።
ከጥቂት አመታት በኋላ ደግሞ 2009 ሁለቱም በአንድ ሳምንት ውስጥ ሊቨርፑልን ለቀው ሪያል ማድሪድን ተቀላቅለዋል።
ዣቢ አሎንሶ ቀድመው ሪያል ማድሪድን 2014 በመልቀቅ ወደ ባየር ሙኒክ ያቀኑ ሲሆን አርቤሎኣ ሁለት አመት በማድሪድ ቆይተዋል።
ስፔንን ወክለው በ 38 ጨዋታዎች ሜዳውን የተጋሩት ሁለቱ አሰልጣኞች በጋራ አውሮፓ ዋንጫ 2x እና አለም ዋንጫ አሸንፈዋል።
ሁለቱም 2016/17 የውድድር ዘመን መጨረሻ ጫማቸውን ሰቅለው ነበር።
አሎንሶ 2018 በሪያል ማድሪድ አካዳሚ የአሰልጣኝነት ስራ ሲጀምሩ አርቤሎኣም ከሁለት አመት በኋላ ወደዚሁ አካዳሚ ሄደዋል።
ዣቢ አሎንሶ ቀጥለው ሪያል ሶሴዳድ ሁለተኛ ቡድን እና ባየር ሌቨርኩሰንን በአሰልጣኝነት መርተው ስኬታማ ጊዜ አሳልፈዋል።
አርቤሎኣ በበኩላቸው የሪያል ማድሪድን ሁለተኛ ቡድን እና ዋናውን ቡድን ማሰልጠን ችለዋል።
ሁለቱ አሰልጣኞች ባለፈው አመት ለስድስት ወራት በሪያል ማድሪድ ልምምድ ማዕከል በቅርበት ሲሰሩ ቆይተዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe