ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ኢንተር ሚያሚን ለመቀላቀሌ አንዱ ምክንያት ሜሲ ነው ” ካሴሚሮ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ኢንተር ሚያሚን ለመቀላቀሌ አንዱ ምክንያት ሜሲ ነው ” ካሴሚሮ
“ ኢንተር ሚያሚን ለመቀላቀሌ አንዱ ምክንያት ሜሲ ነው ” ካሴሚሮ

ብራዚላዊው አማካይ ካሴሚሮ ኢንተር ሚያሚን ስለመረጠበት ምክንያት አስተያየቱን ሰጥቷል።

ሎስ አንጀለስ ጋላክሲ አነጋግሮት እንደነበር የገለፀው ካሴሚሮ አሜሪካ ከሄድኩ ለኢንተር ሚያሚ ብቻ እንደምጫወት ነግሬያቸዋለሁ ብሏል።

“ ክለቡ ያለው አቅድ እና የማሸነፍ ፍላጎት እንዲሁም በታሪክ ከታዩ ምርጥ ተጨዋቾች ከአንዱ ሜሲ ጋር የመጫወት እድል ማግኘቴ ወደ ክለቡ ስቦኛል “ ሲል ካሴሚሮ ተናግሯል።

አክሎም “ ቡድኑን እና ሊዮኔል ሚሴን ሜዳ ላይ ለማገዝ ጓጉቻለሁ “ ሲል ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች