ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

እንግሊዝ ዳግም ራይስን አግኝታለች !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
እንግሊዝ ዳግም ራይስን አግኝታለች !
እንግሊዝ ዳግም ራይስን አግኝታለች !

ከአንድ ጨዋታ እረፍት በኋላ የሶስቱ አናብስት አማካይ ዴክላን ራይስ ወደ ቡድኑ አሰላለፍ ተመልሷል።

ዴክላን ራይስ በዛሬው ጨዋታ ከአሌዮት አንደርሰን ጋር በመጣመር የመሀል ሜዳውን ይመራል።

ቶማስ ቱሄል ራይስን ወደ ቋሚነት መመለስ የዲሞክራቲክ ኮንጎን ፈጣን መልሶ ማጥቃት በጥሩ ሁኔታ ለመመልከት ያለመ ይመስላል።

ራይስ ከክለቡ አርሰናል ጋር ፕሪሚየር ሊጉን በማሸነፍ  ስኬታማ የውድድር አመት አሳልፏል።

ዴክላን ራይስ ለሀገሩም ከሀሪ ኬን ቀጥሎ ያለ ጥርጥር የቡድኑ በጣም አስፈላጊው ተጨዋች ነው።

ቶማስ ቱሄል የመሐል ሜዳቸውን በጋራ ከ 200 ሚልዮን ፓውንድ በላይ ዋጋ ባላቸው ሁለት አማካዮች አዋቅረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች