“ ከቻይና ያገኘሁት ገንዘብ ግዙፍ ነበር ” ኦስካር

“ ከቻይና ያገኘሁት ገንዘብ ግዙፍ ነበር ” ኦስካር
“ ስኖር የነበረው በጉርሻው ብቻ ነበር ”
በለጋ እድሜው ወደ ቻይና አምርቶ ሰባት አመታት ያሳለፈው ኦስካር በጉርሻ ነበር ህይወቴን የምገፋው ሲል ተናግሯል።
በቻይና ከፍተኛ ተከፋይ የነበረው ኦስካር “ ሙሉ ቤተሰቤ በየጨዋታው ከማገኘው ጉርሻ ብቻ ነበር በቅንጦት የሚኖረው ” ብሏል።
“ ዋናውን ደሞዜን በተለየ አካውንት ነበር የማስቀምጠው “ ያለው ኦስካር " እኔና ቤተሰቤ በጨዋታ ጉርሻ ነበር የምንኖረው ምክንያቱም ገንዘቡ ግዙፍ ነበር ” ብሏል።
ገንዘቡ ሲቀርብለት ሁለት ቀን እንዳልተኛ የገለፀው ኦስካር “ ባለቤቴ ነገ እግርህ ቢሰበርስ ተቀበል ሁለት አመት ተጫውተህ ትመለሳለህ ቤተሰብህን አይ ስትለኝ ተቀብያለሁ "ብሏል።
ኦስካር ከዚህ በፊት የቤተሰቡን የወደፊት ህይወት የተሻለ ለማድረግ ከአውሮፓ ለቆ ወደ ቻይና እንዳመራ ገልፆ ነበር።
ኦስካር በቻይና ሊግ በነበረው የሰባት አመታት ቆይታ 175 ሚልዮን ፓውንድ መሰብሰቡ ሲነገር ነበር።
@tikvahethsport @kidusyoftahe