ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ከዘር አጥፊ ጋር ልንጫወት ነው ” አሰልጣኝ ሄሚር ሀልግሪምሰን

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ከዘር አጥፊ ጋር ልንጫወት ነው ” አሰልጣኝ ሄሚር ሀልግሪምሰን
“ ከዘር አጥፊ ጋር ልንጫወት ነው ” አሰልጣኝ ሄሚር ሀልግሪምሰን

“ ያልተማረ እና ግብዝ ከሆነ አሰልጣኝ ጋር ልንጫወት ነው ” እስራኤል

በ አውሮፓ ኔሽንስ ሊግ እስራኤል ከአየርላንድ ጋር ከቀናት በኋላ እንዲጫወቱ መርሐ ግብር ወጥቶላቸዋል።

ይሁን እንጂ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ምክንያት ውዝግብ ውስጥ ገብቷል።

የአየርላንድ አሰልጣኝ ሄሚር ሀልግሪምሰን “ ከዘር አጥፊ ጋር ልንጫወት ነው “ ሲሉ ተናግረው ነበር።

አክለውም “ አሁንም ድረስ ሩሲያ ታግዳ እስራኤል ለምን እንዳልታገደች ማብራሪያ አላገኘሁም " ብለዋል።

የእስራኤል እግርኳስ ፌዴሬሽን በበኩሉ በሰጠው ምላሽ “ የአየርላንድ አሰልጣኝ ላሳየው አለማወቅ እና ግብዝነት መድኃኒት አላገኘንም “ ብሏል።

ፌዴሬሽኑ አክሎም “ አለመማርን ፤ ድድብና ኤና ግብዝነትን ከሚወክል አሰልጣኝ ጋር እንጫወታለን "ሲል ፅፏል።

ዛሬ በአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን ሆቴል የተገኙ ደጋፊዎች ብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታውን እንዳያደርግ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም 160 ያህል የአየርላንድ ስፖርተኞች ጨዋታው እንዳይደረግ ፊርማ አሰባስበው አስገብተዋል።

ጨዋታው እሁድ ምሽት 3:45 በሀንጋሪ እንዲካሄድ መርሐ ግብር ወጥቶለታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች