ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ከደገፋችሁኝ ፍፃሜው እናንተ ጋር ይደረጋል ” ጂያኒ ኢንፋንቲኖ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ከደገፋችሁኝ ፍፃሜው እናንተ ጋር ይደረጋል ” ጂያኒ ኢንፋንቲኖ
“ ከደገፋችሁኝ ፍፃሜው እናንተ ጋር ይደረጋል ” ጂያኒ ኢንፋንቲኖ

የአለም እግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪ ፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በአሁኑ ሰዓት ጫና ውስጥ ወድቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ በሃላፊነት ለመቀጠል የተለያዩ ሀገራትን ድጋፍ እየጠየቁ ሲሆን ሞሮኮም ድጋፍ እንድትሰጣቸው እጅ መንሻ አቅርበዋል።

ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ሞሮኮ በሀላፊነት እንዲቆዩ ከረዳቻቸው በምላሹ የአለም ዋንጫ ፍፃሜን ወደ ራባት እንደሚወስዱ ቃል መግባታቸው ተገልጿል።

ሞሮኮ የ 2030 አለም ዋንጫን ከስፔን እና ፖርቹጋል ጋር በጣምራ እንደምታዘጋጅ ይታወቃል።

የ 2030 አለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ የት ሀገር ይካሄዳል የሚለው እስካሁን ውሳኔ አልተሰጠበትም።

@tikvahethsport          @YisakAH

ተዛማጅ ታሪኮች