ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ከፍፃሜ በፊት የሚደረግ ፍፃሜ : ስፔን ከ ፈረንሳይ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ከፍፃሜ በፊት የሚደረግ ፍፃሜ : ስፔን ከ ፈረንሳይ
ከፍፃሜ በፊት የሚደረግ ፍፃሜ : ስፔን ከ ፈረንሳይ

በአለም ዋንጫው ካሉ ምርጥ ቡድኖች መካከል ስፔን እና ፈረንሳይ መርሐ ግብራቸው ከሰዓታት በኃላ ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ ያካሂዳሉ።

“ ከፍፃሜ በፊት የተደረገ የፍፃሜ ጨዋታ “ እንደሆነ የሚነገርልት ይህ መርሐ ግብር በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።

ጠንካራ የተከላካይ ክፍል እንዳላት ያሳየችው ስፔን አስፈሪ የማጥቃት አቅም ካላት ፈረንሳይ የሚያደርጉት ጨዋታም ይሆናል።

የዲድዬ ዴሾ ቡድን በውድድሩ ምርጥ የፊት መስመር ክፍል እንዳለው እና ለየትኛው ተከላካይ ክፍል ለማቆም ፈታኝ እንደሆነ አሳይቷል።

ይህን ለማቆም ከቻለች ደግሞ ስፔን ልትሆን እንደምትችል በውድድሩ ያላት ቁጥር ይናገራል።

አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርባት የተጓዘችው ስፔን በቤልጅዬም ጨዋታ ብቻ በ ዲ ካትሌይር አማካኝነት አንድ ግብ ሊቆጠርባት ችሏል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች