የሀሪ ኬን የወርቅ ጨማ ፉክክር ?

የሀሪ ኬን የወርቅ ጨማ ፉክክር ?
የ 2018 አለም ዋንጫ የወርቅ ጫማ አሸናፊ ሀሪ ኬን በዚህ አመትም በፉክክሩ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
ሀሪ ኬን በመጀመሪያ ጨዋታው ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር ጥሩ አጀማመር አድርጎ ነበር።
ይሁን እንጂ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታ ግብ አለማስቆጠሩን ተከትሎ ከፉክክሩ ወደ ኋላ ቀርቷል።
ከመጀመሪያው ጨዋታ በኋላ በፉክክሩ የነበሩ ተጨዋቾች አሁን ላይ የግብ መጠናቸውን ከፍ አድርገዋል።
ሀሪ ኬን በወርቅ ጫማ አሸናፊነት ፉክክሩ ለመቆየት በዛሬው ጨዋታ ግቦችን ማስቆጠር ይጠበቅበታል።
በአሁኑ ሰዓት አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በ 5️⃣ ጎል ኮከብ ግብ አግቢነቱን እየመራ ይገኛል።
በተጨማሪም:-
4️⃣ ጎሎች :- ኪሊያን ምባፔ ፣ ኤርሊንግ ሀላንድ ፣ ቪንሰስ ጁኒየር እና ኡስማን ዴምቤሌ
3️⃣ ጎሎች :- ስምንት ተጨዋቾች
2️⃣ ጎሎች :- ሀሪ ኬን እና ሮናልዶን ጨምሮ 21 ተጫዋቾች በኮከብ ግብ አግቢነት ፉክክር ላይ ይገኛሉ።
@tikvahethsport @kidusyoftahe