ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የማንችስተር ሲቲ የዝውውር ሁኔታ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የማንችስተር ሲቲ የዝውውር ሁኔታ ?
የማንችስተር ሲቲ የዝውውር ሁኔታ ?

ማንችስተር ሲቲዎች ኤሊየት አንደርሰንን በከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ የግላቸው ለማድረግ ተስማምተዋል።

ከአስር አመታት በኋላ ፔፕ ጋርዲዮላን ያጣው ክለቡ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን ተተኪ አድርጎ ቀጥሯል።

የዝውውር መስኮቱ ማንችስተር ሲቲ ተጨዋች በመሸጥ እና መግዛት የሚወጠርበት እንደሚሆን ተገልጿል።

ክለቡ ባለፉት ወራት ቡድኑን ለመገንባት ያመጣቸው አዲስ ተጨዋቾች በዚህ ክረምት ሊለቁ ይችላሉ።

ይህም ማለት ማንችስተር ሲቲ የለቀቁ ተጨዋቾችን በአዲስ ለመተካት በርካታ ዝውውሮች ሊያደርግ ይችላል።

ማንችስተር ሲቲ በቀጣይ የቀኝ መስመር ፤ አማካይ እና የክንፍ ቦታዎችን ቅድሚያ ሰጥቶ ለማጠናከር ማቀዱ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፊል ፎደን ፣ ጄርሚ ዶኩ እና ግቫርዲዮል በቀጣይ ሳምንታት ውላቸውን ያራዝማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport          @YisakAH

ተዛማጅ ታሪኮች