የምሽቱ ጨዋታ የአየር ሁኔታ አስግቷል !

የምሽቱ ጨዋታ የአየር ሁኔታ አስግቷል !
የምሽቱ የፈረንሳይ እና ፓራጓይ ጨዋታ በታሪክ በከፍተኛ ሙቀት የሚደረግ ጨዋታ እንደሚሆን ተነግሯል።
ጨዋታው በሚደረግበት አሜሪካ ፊላደልፊያ በከፍተኛ ሙቀት ይመታል በሚል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
በአካባቢው ይኖራል ተብሎ የሚጠበቀው ሙቀት ሪከርድ ሆኖ ከተመዘገበው ( 39°C ) በትንሽ ያነሰ 38°C መሆኑ ተገልጿል።
ይሁን እንጂ ሜዳ ላይ የሚኖረው የሙቀት መጠን ከዚህም የከፋ ሊሆን እንደሚችል እና 43°C ሊደርስ እንደሚችል ተነግሯል።
ለሁለቱ ቡድን ተጨዋቾች መልካሙ ዜና ሜዳው የተፈጥሮ ሳር መሆኑና ከሰው ሰራሽ የተሻለ ቀዝቃዛ መሆኑ ነው።
ይሁን እንጂ የሙቀት መጠኑ ( 43°C ) ለተጨዋቾቹ የውስጥ እግር ፈታኝ እንደሚሆን ተነግሯል።
በተጨማሪም ከባድ ነጎድጓድ እና አውሎ ነፋስ ሌላኛው የጨዋታው ስጋት መሆኑ ተዘግቧል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe