ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የብራይተን ቅድመ ውድድር ዝግጅት ተሰረዘ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የብራይተን ቅድመ ውድድር ዝግጅት ተሰረዘ !
የብራይተን ቅድመ ውድድር ዝግጅት ተሰረዘ !

ብራይተን በፈረንሳይ ሊያደርገው አቅዶት የነበረው የቅድመ ውድድር ዝግጅት አለመሳካቱ ተነግሯል።

የዝግጅቱ አለመሳካት ምክንያት የአለም ሀገራት መሪዎች ሄሊኮፕተር ሜዳውን አበላሽቶት መሆኑ ተገልጿል።

የአለም ሀገራት መሪዎች ባለፈው የቡድን-7 ስብሰባ ሜዳውን የሄሊኮፕተር ማቆሚያ በማድረግ ከጥቅም ውጪ ማድረጋቸው ተነግሯል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲሁም የእንግሊዝ እና ፈረንሳይ መሪዎች ሜዳውን ለማቆሚያ ተጠቅመው እንደነበር ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ብራይተን ዝግጅቱን እና ነገ ሊያደርግ የነበረውን የወዳጅነት ጨዋታ በመሰረዝ ወደ ኦስትሪያ ለማቅናት ማቀዱ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች