ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የቪንሰስ ጁኒየር የሪያል ማድሪድ ሁኔታ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የቪንሰስ ጁኒየር የሪያል ማድሪድ ሁኔታ ?
የቪንሰስ ጁኒየር የሪያል ማድሪድ ሁኔታ ?

ሪያል ማድሪድ እና ቪንሰስ ጁኒየር በአሁኑ ሰዓት በአዲስ ውል ዙሪያ መስማማት እንዳልቻሉ ተገልጿል።

የስምምነቱ ትልቅ ችግር የምስል መብት እና የፊርማ ጉርሻ ገንዘብ ዙሪያ መሆኑን ለተጨዋቹ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ዘግበዋል።

አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ከቪንሰስ ጁኒየር ጋር በቀጥታ ለበርካታ ጊዜያት መነጋገራቸው ተገልጿል።

ጆዜ ሞሪንሆ ቪንሰስ ጁኒየር አስፈላጊ መሆኑን ለራሱ በቀጥታ መንገራቸው ተዘግቧል።

ይሁን እንጂ ሪያል ማድሪድ ከስምምነት ካልተደረሰ ሌላ ትልቅ የአውሮፓ ክለብ ወደ ፉክክሩ ይገባል የሚል እምነት አለው ተብሏል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ቪንሰስ ላይ ፍላጎት ያለው አርሰናል ብቻ ነው የሚል እምነት እንደሌላቸው ተዘግቧል።

አርሰናል በበኩሉ የተጫዋቹን የኮንትራት ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች