ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የቼልሲ የዝውውር ሁኔታ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የቼልሲ የዝውውር ሁኔታ ?
የቼልሲ የዝውውር ሁኔታ ?

ሞርጋን ሮጀርስን በከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ ያስፈረሙት ሰማያዊዎቹ አሁንም ተጨዋች ማስፈረማቸውን እንደሚቀጥሉ ተነግሯል።

ይሁን እንጂ ገንዘብ ለማግኘት እና ደንቡን ለመጠበቅ የተጨዋቾች ሽያጭ እንደሚኖር ተገልጿል።

ቼልሲ በዚህ ክረምት እስካሁን ከተጨዋቾች ሽያጭ 1️⃣4️⃣0️⃣ ሚልዮን ፓውንድ ገቢ አግኝተዋል።

ነገርግን ሰማያዊዎቹ የዝውውር መስኮቱ ከመጠናቀቁ በፊት ለመሸጥ ያዘጋጇቸው በርካታ ተጨዋቾች እንዳሏቸው ተነግሯል።

ቼልሲ በዚህ ክረምት ከተጨዋቾች ሽያጭ ከ 3️⃣0️⃣0️⃣ ሚልዮን ፓውንድ በላይ ገቢ ለማግኘት ማቀዱ ተገልጿል።

ክለቡን በቀጣይ ምን ያስፈርማል ?

ቼልሲ የማንችስተር ሲቲውን ተከላካይ ጆን ስቶንስን በተከላካይ ዝርዝር ውስጥ አካተውታል።

ሰማያዊዎቹ በዚህ ክረምት በቡድኑ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉ ዝግጁ ተጨዋቾችን ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

ክለቡ በሽያጭ ላይ ተመርኩዞ ሁለት ዝግጁ የመሐል ተከላካዮች እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ተጨዋቾች ለማስፈረም አቅዷል ተብሏል።

ዘገባው የ ዘ አትሌቲክ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች