ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የኖርዌይ የቡድን ጥንካሬ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የኖርዌይ የቡድን ጥንካሬ ?
የኖርዌይ የቡድን ጥንካሬ ?

ኖርዌይ ከተወሰኑ ተጨዋቾች በቀር ልክ እንደ እንግሊዝ ጥራት ባላቸው ኮከቦች የተሞላ ቡድን የላትም።

ይሁን እንጂ ኖርዌይ እንደ ቡድን ያላት ጥንካሬ እንግሊዝን ማሸነፍ የሚያስችላት እንደሆነ ይነሳል።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የመሀል ሜዳ ለዚህ እንደ ማሳያው ተደርጎ መታየት ይችላል።

እንግሊዝ የመሀል ሜዳዋ ውድ ዋጋ ባለቸው እና ትልቅ ስም በያዙ ሶስት አማካዮች ተዋቅሯል።

ይሁን እንጂ ቤሊንግሀም ፣ ራይስ እና አንደርሰን እንደ ቡድን ከሚያደርጉት ይልቅ በግላቸው ጥሩ ነገር ያስመለክታሉ።

በሌላ በኩል የኖርዌይ አማካዮች ኦዴጋርድ ፣ ሳንደር ቤርጌ እና እና ፓትሪክ ቤርግ ያን ያህል ውድ ዋጋ የላቸውም።

ነገርግን ሶስቱ ተጨዋቾች በጋራ ሲጫወቱ ጠንካራ ሲሆኑ አንዱ የአንዱን ጥንካሬ ሲጠቀም ያላቸውን ድክመት ይሸፋፈናሉ።

በተጨማሪም ኖርዌይ የግለሰብ ብቃት ለውጥ እንደሚያመጣ በተደጋጋሚ ያስመሰከረውን ሀላንድ ይዛለች።

ኤርሊንግ ሀላንድ እንግሊዝ ከያዘቻቸው ተከላካዮች የበለጠ ጠንካራ የሆኑትን ተጋፍጦ የበላይ መሆን ችሎ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች