ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የአልቫሬዝ የአትሌቲኮ ማድሪድ ሁኔታ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የአልቫሬዝ የአትሌቲኮ ማድሪድ ሁኔታ ?
የአልቫሬዝ የአትሌቲኮ ማድሪድ ሁኔታ ?

አርጀንቲናዊው አጥቂ ጁሊያን አልቫሬዝ አትሌቲኮ ማድሪድን ለመልቀቅ ጥያቄ ካቀረበ በኋላ ትላንት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሜዳ ተመልሷል።

ይሁን እንጂ ጁሊያን አልቫሬዝ ከክለቡ ደጋፊዎች ከፍተኛ ተቃውሞ እና ስድብ አስተናግዶ ወጥቷል።

አልቫሬዝ ጨዋታው ሲያበቃም ከቡድን አጋሮቹ ጋር ወደ ደጋፊዎቹ ሳይቀርብ ቀጥታ ወደ መልበሻ ቤት አቅንቷል።

አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒ ከጨዋታው በኋላ አልቫሬዝ ከቡድን አጋሮቹ ጋር ወደ ደጋፊዎች ያልቀረበው በክለቡ ውሳኔ መሆኑን ተናግረዋል።

አልቫሬዝ አሁንም ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ እና ባርሴሎናን መቀላቀል ህልሙ እንደሆነ ለተጨዋቹ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ገልጸዋል።

ተጨዋቹ ለባርሴሎናም ቁጥር አንድ ኢላማ ቢሆንም አትሌቲኮ ማድሪድ ለባርሴሎና መሸጥ አይፈልግም።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በበኩሉ የጁሊያን አልቫሬዝን ለማስፈረም ለረጅም ጊዜ እየፈለገ ይገኛል።

አትሌቲኮ ማድሪድ ተጨዋቹ አይሸጥም ሲል የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ 150 ሚልዮን ዩሮ ከቀረበ ሊሸጠው ይችላል ተብሏል።

ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን ለተቀናቃኞቹ ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ የመሸጠ ፍላጎት የላቸውም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ 150 ሚልዮን ዩሮ ከአርሰናል ከቀረበ ግን ክለቡ ተጫዋቹን ሊሸጠው እንደሚችል ተነግሯል።

መድፈኞቹ ግን እስካሁን ገንዘቡን እንዳላቀረቡ እና ይህን ያህል ገንዘብ ያቀርባሉ ተብሎ እንደማይጠበቅ ተነግሯል።

ዘገባው የ ዘ አትሌቲክ ነው።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች