ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የዩናይትድ ደጋፊዎች ተቃውሞ ሊያደርጉ ነው !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የዩናይትድ ደጋፊዎች ተቃውሞ ሊያደርጉ ነው !
የዩናይትድ ደጋፊዎች ተቃውሞ ሊያደርጉ ነው !

የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች በዛሬው የደርቢ ጨዋታ ዕለት ተቃውሞ ለማሰማት ቀጠሮ ይዘዋል።

ደጋፊዎቹ በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ውጪ እና ውስጥ ተቃውሞ ለማሰማት ማቀዱን ገልጿል።

ደጋፊዎቹ በስታዲየሙ ውስጥ የሚገኘውን አርማ ለማውረድ ማቀዳቸውንም ገልጸዋል።

በምትኩ “ እኛን የያዛችሁበት መንገድ አሳፋሪ ነው ” የሚል ፅሁፍ ለማስመልከት እቅድ መያዛቸው ተነግሯል።

ደጋፊዎቹ አርማው በቀጥታ ስርጭት እንዲታይ የተጨዋቾች መውጫ ላይ ለማስቀመጥ ማቀዳቸው ተዘግቧል።

ተቃውሞው የትኬት ጭማሬ እና ሌሎች ጉዳዮችን የተመለከተ እንደሆነ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች