የፍፃሜ ጨዋታው ዳኛ ማን ናቸው ?

የፍፃሜ ጨዋታው ዳኛ ማን ናቸው ?
የምሽቱን የአለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ስሎቬኒያዊው ዳኛ ስላቭኮ ቪንቺች እንዲመሩ ተመርጠዋል።
ስላቭኮ ቪንቺች በሪያል ማድሪድ እና ዶርትመንድ መካከል የተደረገውን የ 2024 ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ መርተው ነበር።
የ 46ዓመቱ ዳኛ የአለማችን ትልቁን የእግር ኳስ ጨዋታ በመምራት የመጀመሪያ ስሎቬኒያዊ ይሆናሉ።
ዳኛው ባለፈው ሀሙስ በጨዋታው መመደባቸውን ሲሰሙ በእንባ ታጅበው ነበር ደስታቸውን የገለፁት።
“ መጀመሪያ ደንግጬ ነበር በኋላ ግን ተደስቻለሁ ፤ የአለም ዋንጫ ፍፃሜ መምራት ለእኔ ክብር ነው ” ሲሉ ዳኛው ስሜታቸውን ይገልፃሉ።
በ 2022 አርጀንቲና በሳውዲ አረቢያ 2ለ1 ስትሸነፍ የጨዋታው ዳኛ ስላቭኮ ቪንቺች ነበሩ።
በሌላ በኩል በሶስት አጋጣሚዎች የስፔንን ጨዋታ ሲመሩ ስፔን ሁሉንም ጨዋታዎች አሸንፋለች።
ሁለተኛ የአለም ዋንጫ ተሳትፎ ያደረጉት ዋና ዳኛው በዚህ ውድድር አራተኛ ጨዋታቸው ይሆናል።
ፊፋ ከዚህ በፊት የፍፃሜ ጨዋታውን የሚመራ ዳኛ የሚመርጠው ከቡድኖቹ አህጉር ውጪ የሆነ ዳኛ ነበር።
ይሁን እንጂ ስላቭኮ ቪንቺች በዳኞች ሀላፊው ኮሊና ትልቅ ቦታ ስለሚሰጣቸው እንደተመረጡ ተነግሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe