ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ያማል ከአለም ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ ነው ” ሊዮኔል ሜሲ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ያማል ከአለም ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ ነው ” ሊዮኔል ሜሲ
“ ያማል ከአለም ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ ነው ” ሊዮኔል ሜሲ

አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ከአመታት በፊት ከላሚን ያማል ጋር ስላላቸው ታዋቂ ፎቶ አንስቷል።

“ በልጅነቱ አብረን ያለን ፎቶ የሚደንቅ ነው “ ያለው ሜሲ አሁን እርስበርስ ልንጫወት ነው ህይወት ባልተጠበቁ ነገሮች የተሞላች ነች “ ሲል ገልጿል።

አክሎም “ ያማል በአሁኑ ሰዓት ከአለም ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ ነው ፤ እኛ ባርሴሎናዎች እሱ ስላለን እድለኞች ነን ጥሩ ነገር እመኝለታለሁ "ብሏል።

በፍፃሜው “ ጥሩ ጨዋታ ለማድረግ እንሞክራለን ነገርግን ያማል እና የቡድን አጋሮቹ በምርጥ አቋማቸው ላይ እንደማይሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ “ ሲል ተናግሯል።

“ ስፔን በርካታ ጥሩ ተጨዋቾች አሏት እነሱን ማቆም አለብን “ ሊዮኔል ሜሲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች