“ ይሄ ቡድን አንገታችሁን አያስደፋችሁም ” ሜሲ

“ ይሄ ቡድን አንገታችሁን አያስደፋችሁም ” ሜሲ
“ ምንም የተሰጠን ነገር የለም የተበሳጨ ሁሉ ይበሳጭ ”
አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ቡድኑ የሀገሪቱን ህዝብ አንገት አያስደፋም በማለት ተናግሯል።
ለአርጀንቲና ህዝብ ኳታር ላይ እንዳልኩት አሁንም “ ተዝናኑ ይሄ ቡድን መቼም አንገታችሁን አያስደፋችሁም ማለት እፈልጋለሁ ” ብሏል።
“ ማራዶና በዚህ እንደተደሰተ እርግጠኛ ነኝ ድሉ ለእሱ ነው ” ያለው ሜሲ እሱ ለሰጠን ጊዜ እድለኞች ነን ራሴን ከእሱ ጋር አላወዳድርም ብሏል።
“ ማንም ሰው ምንም ነገር አልሰጠንም ባለፉት አራት አመታት ምርጥ ቡድን ነበርን የተበሳጨ ሁሉ መበሳጨት ይችላል “ ሊዮኔል ሜሲ
ስለ ፍፃሜው ያነሳው ሜሲ “ ስፔን አስደናቂ ብሔራዊ ቡድን ነው አጨዋወታቸውን በደንብ አውቀዋለሁ ” ሲል ገልጿል።
አክሎም “ ለአመታት የተከተሉት የጨዋታ መንገድ አላቸው ብዙዎቹ ለምወደው ክለብ ባርሴሎና ይጫወታሉ ፤ ተመጣጣኝ ጨዋታ ይሆናል ” ብሏል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe