ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ይሄ የመጨረሻ አመቴ መሆኑን አላውቅም “ ሮናልዶ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ይሄ የመጨረሻ አመቴ መሆኑን አላውቅም “ ሮናልዶ
“ ይሄ የመጨረሻ አመቴ መሆኑን አላውቅም “ ሮናልዶ

ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በብሔራዊ ቡድኑ እስከመቼ እንደሚቆይ " አላውቅም " ሲል ተናገረ።

“ የዛሬን ነው የምኖረው ለረጅም ጊዜ አላስብም ” ያለው ሮናልዶ “ የመጨረሻ አመቴ ነወይ ? ለሚለው ምናልባት ፤ ግን እናያለን " ብሏል።

“ በአካላዊ ሁኔታዬ እና ፅናቴ ላይ የተመሰረተ ነው ፤ እውነቱን ለመናገር አላውቅም ይሄን የምለው ከልቤ ነው “ ሲል ሮናልዶ የተናገረው።

አክሎም “ አሰልጣኙ እኔ ካላስፈለኩት መሄድ እችላለሁ ጊዜው ሲደርስ እኔ ራሴ አነጋግረዋለሁ ” ብሏል።

“ ለቡድኑ አስተዋጽኦ እያደረግኩ እንዳልሆነ ከተሰማኝ ሻንጣዬን አንስቼ እሄዳለሁ " ሲል ክርስቲያኖ ሮናልዶ ተናግሯል።

ሮናልዶ በቀጣይ አላማው 1,000 ግቦች ላይ መድረስ እና ኔሽን ሊግ ዋንጫ ማሸነፍ መሆኑን ገልጿል።

አሰልጣኝ ጆርጅ ጄሱስ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በነገው የዌልስ ጨዋታ በቋሚነት እንደሚሰለፍ አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች