ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ደጋፊዎች የሮናልዶ መስሏቸው ሌላ ሰርግ ታደሙ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ደጋፊዎች የሮናልዶ መስሏቸው ሌላ ሰርግ ታደሙ !
ደጋፊዎች የሮናልዶ መስሏቸው ሌላ ሰርግ ታደሙ !

ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ጆርጂና በዛሬው ዕለት የጋብቻ ስነስርዓታቸውን በማዴራ እንደሚያደርጉ ሲዘገብ ነበር።

ይሁን እንጂ ተጋቢዎቹ የሰርግ ስነ ስርዓቱ በዛሬው ዕለት ስለመደረጉ በይፋ ምንም ያሉት ነገር አልነበረም።

ዜናውን ያነበቡ በርካታ ደጋፊዎች ግን የሰርግ ስነስርዓቱ ይካሄድበታል ተብሎ ወደ ተነገረው ቤተክርስቲያን አቅንተው ነበር።

ደጋፊዎቹ ውጪ ላይ ሮናልዶ እና ጆርጂናን ለማየት ሲጠብቁ ሙሸሮቹ ሌሎች የአካባቢው ጥንዶች ሆነው አግኝተዋቸዋል።

ደጋፊዎቹ ውስጥ የሚደረገው የሰርግ ስነስርዓት የክርስቲያኖ ሮናልዶ መስሏቸው እንደነበር ተገልጿል።

አንድ የሰርጉ ተካፋይ “ ይሄ ሁሉ ሰው ሮናልዶ ያለ ፀጥታ ጥበቃ እዚህ ያገባል ብሎ ማሰቡ አስደንቆኛል “ ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport          @YisakAH

ተዛማጅ ታሪኮች