“ ዶናልድ ትራምፕ እርዳታህን እፈልጋለሁ “

“ ዶናልድ ትራምፕ እርዳታህን እፈልጋለሁ “
የአለም ዋንጫን ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር በ 2010 ማሳካት የቻለው ሁዋን ካፕ ዴቪያ ወደ አሜሪካ መጓዝ እንዳልቻለ ገልጿል።
ካፕ ዴቪያ የቡድን አጋሮቹ በቀረበላቸው ጥሪ ቡድናቸውን ለመደገፍ ወደ አሜሪካ ሲያቀኑ ቪዛ ማግኘት ባለመቻሉ ከጉዞ ቀርቷል።
ካፕ ዴቪያ በ 2016 በኢራን ሀገር ገብቶ ጨዋታ ማድረጉን ተከትሎ ቪዛ ሊያገኝ አለመቻሉን ገልጿል።
“ ከልጆቼ ጋር ወደ አሜሪካ መጓዝ እንደማልችል ተነግሮኛል ፣ ከ 2010 የአለም ዋንጫ የቡድን አጋሮቼ ጋር በመሆን ሀገሬን ለመደገፍ ጓጉቼ ነበር “ ሲል ካፕ ዴቪያ ከ ክልከላው በኃላ ተናግሯል።
አክሎም ለአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጥሪ ሲያቀርብ “ ዶናልድ ትራምፕ እርዳታ እፈልጋለሁ “ ሲልም መልዕክቱን አጋርቷል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe