ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ፊፋ የጨዋታውን ዳኛ ሊያግድ ይችላል ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ፊፋ የጨዋታውን ዳኛ ሊያግድ ይችላል ?
ፊፋ የጨዋታውን ዳኛ ሊያግድ ይችላል ?

ግብፅ የትላንቱን ጨዋታ የመሩት ዳኞች ላይ ምርመራ እንዲደረግ ለፊፋ በይፋ ቅሬታ አቅርባለች።

ግብፅ ሁለተኛ ጎላቸው ለምን እንደተሻረ እና አርጀንቲና ሶስተኛ ጎል ስታስቆጥር የነበረው ክስተት እንዲጣራ ጠይቃለች።

በተጨማሪም የጨዋታው ፈረንሳዊ የመሐል ዳኛ ፍራንኮይስ ሌቴዤር ከውድድሩ እንዲታገዱ ጥያቄ አቅርባለች።

ፊፋ በበኩሉ የቀረበውን ቅሬታ አይቶ ዳኛውን ከውድድሩ ያግዳል ተብሎ እንደማይጠበቅ ተገልጿል።

አወዳዳሪው አካል ፊፋ የዳኛውን የጨዋታ አፈፃፀም እንደሚገመገም ተነግሯል።

በሌላ በኩል ፈረንሳይ በውድድሩ የምታደርገው ጉዞ ታይቶ ዳኛው በቀሪ ጨዋታዎች ላይመደቡ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ዳኛው ከጨዋታው በኋላ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸውን በጊዜያዊነት ከእይታ ደብቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች