ፔድሮ ኔቶ ወዴት ሊያመራ ይችላል ?

ፔድሮ ኔቶ ወዴት ሊያመራ ይችላል ?
የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል የቼልሲውን ተጨዋች ፔድሮ ኔቶ ኢላማ ማድረጉ ተገልጿል።
አል ሂላል ማልኮም ክለቡን መልቀቁን ተከትሎ ፔድሮ ኔቶን ተተኪ የማድረግ እቅድ እንዳላቸው ተዘግቧል።
በሌላ በኩል ማንችስተር ሲቲ ፔድሮ ኔቶን እንደሚያደንቁ እና ወኪሎቹን አነጋግሮ እንደነበር ተገልጿል።
ይሁን እንጂ የማንችስተር ሲቲ ሀላፊዎች ቼልሲ ተጫዋቹን ለመሸጥ ያስቀመጠው ሂሳብ ከፍተኛ ነው የሚል እምነት አላቸው።
በዚህም ምክንያት የፔድሮ ኔቶ መዳረሻ ሳውዲ አረቢያ ሊሆን እንደሚችል ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል።
በሌላ በኩል ማንችስተር ሲቲ በኢንዞ ፈርናንዴዝ ዝውውር ዙሪያ አሁንም ተስፋ እንዳልቆረጠ ተገልጿል።
ማንችስተር ሲቲ በሚቀጥለው ሳምንት አዲስ ንግግር ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe