ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#PremierLeague

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#PremierLeague
#PremierLeague

በአሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የሚመራው ቼልሲ በሊጉ በርካታ ጎሎችን ካሳዩን ክለቦች መካከል በቀዳሚነት ይገኛል።

በሊጉ አራት የቼልሲ ጨዋታዎች 1️⃣9️⃣ ጎሎችን መመልከት ችለናል።

ከደቂቃዎች በኃላ በሚጀምረው መርሐ ግብር ሰማያዊዎቹ ያለ አጥቂያቸው ጇ ፔድሮ ወደ ሜዳ የሚገቡ ይሆናል።

አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ከ ሁል ሲቲ ጋር 2-2 ከወጣው ስብስባቸው የአምስት ተጫዋቾችን ቅያሪ አድርገው ገብተዋል።

ከእነዚህም መካከል :-

- ጆርዳን ሄንደርሰን የቀድሞ ክለቡን ለመግጠም በቋሚነት ጨዋታውን ይጀምራል።

- ዳኒ ዌልቤክ ለጨዋታው ብቁ ያልሆነውን ጇ ፔድሮ ተክቶ የምንመለከተው ይሆናል።

አሰልጣኝ ኪት አንድሪውስ በበኩላቸው ካለፈው የሊጉ ጨዋታቸው የሁለት ተጫዋቾችን ቅያሪ አድርገዋል።

ሚሼል ካዮዴ እና ሚኬል ዳምስጋርድ በብሬንትፎርድ በኩል የምንመለከተው ለውጥ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች