" ልዩ ድል ነው ፤ በቡድኔ ኮርቻለሁ " ፋብያን ሁርዜለር

" ልዩ ድል ነው ፤ በቡድኔ ኮርቻለሁ " ፋብያን ሁርዜለር
የብራይተኑ አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር አርሰናል ላይ ከተቀዳጁት ድል በኋላ “ በቡድኔ ኮርቻለሁ ” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
“ ልዩ ድል ነው “ ሲሉ የገለፁት ፋብያን ሁርዜለር “ ያሸነፍነው የእንግሊዙን ምርጥ ቡድን ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ያሳየነው አቋም ልዩ ያደርገዋል ” ብለዋል።
አክለውም “ በቡድኔ በጣም ኮርቻለሁ ፤ ለተጋጣሚያችን በጣም አስፈሪ ነበርን " በማለት ተናግረዋል።
ስለ ቡድናቸው አምበል ፓስካል ግሮስ ያነሱት አሰልጣኙ “ ግቦችን በማስቆጠር የሚደሰት ” ሲሉ ገልፀውታል።
“ ሙሉ በሙሉ ልታምነው የምትችለው እና በዙሪያው ያሉትን የቡድን አጋሮቹን በእጅጉ የተሻሉ የሚያደርግ ተጫዋች ነው “ ሲሉ አወድሰውታል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe