ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ማንችስተር ሲቲ ምን አይነት ሰነድ አቀረበ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ማንችስተር ሲቲ ምን አይነት ሰነድ አቀረበ ?
ማንችስተር ሲቲ ምን አይነት ሰነድ አቀረበ ?

ማንችስተር ሲቲ የፕሪሚየር ሊጉን የፋይናንስ ደንብ በመጣስ ጥፋተኛ መባሉን ተከትሎ ይግባኝ ጠይቋል።

የክለቡ ዋና ሀላፊ ሶሪያኖ ለክለቡ ሰራተኞች በላኩት መልዕክት ክሱ በሀሰተኛ ውንጀላ ላይ የተንተራሰ ነው ብለው ነበር።

የሊጉ ክስ ጭብጥ የማንችስተር ሲቲ ባለቤቶች ስፖንሰሮችን በመጠቀም ገንዘብ ወደ ክለቡ አስገብተዋል የሚል ነው ሲሉ ሀላፊው ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ማንችስተር ሲቲ ስፖንሰሮቹ ገንዘቡን ያገኙት ከክለቡ ባለቤቶች ሳይሆን ከአቡዳቢ መንግሥት መሆኑን ገልጿል።

ማንችስተር ሲቲ አሁን ላይ የክለቡ ስፖንሰሮች ገንዘብ ከአቡዳቢ መንግሥት ሲጠይቁ የሚያሳይ ሰነድ ለሊጉ ማቅረቡ ተገልጿል።

ስፖንሰሮቹ ተጨማሪ የስፖንሰር ክፍያ ገንዘብ ሲያጥራቸው ባለአክሲዮኖችን እንደሚጠይቁ ክለቡ ገልጿል።

የስፖንሰሮቹ ባለአክሲዮኖች ደግሞ የ አቡዳቢ መንግሥት እንጂ የማንችስተር ሲቲ ባለቤት አለመሆኑን አስረድቷል።

ማንችስተር ሲቲ በመንግሥት ሳይሆን በአቡዳቢ ዩናይትድ ግሩፕ በብቸኛ ባለቤትነት መያዙን መግለፁ ተዘግቧል።

ተቋማት የስፖንሰር ወጪ ገንዘብ ለማግኘት ባለአክሲዮኖችን መጠየቃቸው ጤናማ አሰራር ነው ሲል ማንችስተር ሲቲ ተከራክሯል።

ለክለቡ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ማንችስተር ሲቲ ውስጥ ክለቡ ክሱን እንደሚረታ እርግጠኛ መሆኑን የሚያሳይ ስሜት እንዳለ ገልጸዋል።

@tikvahethsport          @YisakAH

ተዛማጅ ታሪኮች