ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ሜሲን ለመግለጽ ቃላት አይታዘዙም ” ጉሌርሞ ሆዮስ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ሜሲን ለመግለጽ ቃላት አይታዘዙም ” ጉሌርሞ ሆዮስ
“ ሜሲን ለመግለጽ ቃላት አይታዘዙም ” ጉሌርሞ ሆዮስ

ኢንተር ሚያሚ ሌሊቱን ከሞንትሬል ያደረገውን የሜጀር ሊግ ሶከር ጨዋታ 7ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።

ሊዮኔል ሜሲ በጨዋታው አራት ግቦችን አስቆጥሮ አንድ ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ በማቀበል ጥሩ ጊዜ አሳልፏል።

ቀሪዎቹን የኢንተር ሚያሚ ጎሎች ካሴሚሮ ፣ ሱዋሬዝ እና ሾው ማስቆጠር ችለዋል።

የኢንተር ሚያሚ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ጉሌርሞ ሆዮስ በሰጡት አስተያየት “ ቃላት ሊዮኔል ሜሲን መግለጽ አይችሉም ” ብለዋል።

አክለውም “ ሊዮኔል ሜሲ አንድ ተራ እግርኳስ ተጨዋች አይደለም ልዩ ነው ” ሲሉ ገልፀውታል።

ካሴሚሮ በበኩሉ “ ሜሲ አሁንም ቢሆን ምርጥ ነው ያንን በአለም ዋንጫው አረጋግጧል ” ብሏል።

“ ከእሱ ጋር መደሰት አለብን ምክንያቱም እሱ ሲኖር የበለጠ ጠንካራ እንሆናለን ” ሲል ጨምሮ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች