ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ቶሚያሱ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ይገኛል !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ቶሚያሱ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ይገኛል !
ቶሚያሱ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ይገኛል !

የቀድሞ የአርሰናል ተከላካይ ታኬሂሮ ቶሚያሱ በአሁኑ ሰዓት ከክሪስታል ፓላስ ጋር ልምምድ እየሰራ ይገኛል።

ከአያክስ ጋር መለያየቱን ተከትሎ ያለ ክለብ የሚገኘው ቶሚያሱ ቀጣይ ማረፊያውን እየተመለከተ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ቶሚያሱ በቀጣይ ለክሪስታል ፓላስ ተሰልፎ የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርግ ይችላል ተብሏል።

ተጫዋቹን ለማስፈረም ከፕሪሚየር ሊግ እና አውሮፓ ክለቦች ፍላጎት እንዳለ ተጠቁሟል።

ጃፓናዊው ተከላካይ ቶሚያሱ በሚቀጥለው አመት ወደ ፕሪሚየር ሊግ መመለስ እንደሚፈልግ ተዘግቧል።

ክሪስታል ፓላስ ተጨዋቹ የአካል ብቃቱን እንዲጠብቅ እና እንዲጠብቅ የልምምድ ቦታ እንዳመቻቹለት ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች