አርሰናል ከናሳ ጋር ይሰራ ነበር !

አርሰናል ከናሳ ጋር ይሰራ ነበር !
አርሰናል ከአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ ጋር መስራቱን የክለቡ የቀድሞ ፐርፎርማንስ ሀላፊ ቶም አለን ተናግረዋል።
የቡድኑ አንዱ ተጨዋች ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት እግሩን መጠቀም ስላልቻለ የናሳ እርዳታ አስፈልጎን ነበር ብለዋል።
ተጨዋቹ የተጎዳ እግሩን ስለማይጠቀም ብዙ ጡንቻ ያጣል የሚል ስጋት እንዳደረባቸው ተናግረዋል።
ሁኔታውን ለመፍታት “ ብዙ ቦታ ረግጠናል ” ያሉት ሀላፊው “ በኋላም ፊታችን ወደ ናሳ ዞረ ” ብለዋል።
ነገሩን ያገናኘነው “ ሰዎች ወደ ህዋ ሲሄዱ የመሬት ስበት ስለሌለ ብዙውን ጊዜ ይንሳፈፋሉ ያ ሁኔታውን ተመሳሳይ ስላደረገው ነው ” ብለዋል።
ይህም ማለት ጠፈርተኞቹ ህዋ ላይ ሲሆኑ ሰውነታቸው የአካል ክብደታቸውን ሳይሸከም እንዲቆይ ያደርጋል።
ይህንንም ተከትሎ አርሰናል ናሳ ጠፈርተኞች ወደ ህዋ ሲልክ በሚንሳፈፉበት ወቅት ጡንቻቸውን እንዳያጡ ምን እንደሚደረግ ጠይቋል።
ከናሳ የስነ ምግብ ባለሙያ ጥሩ ምላሽ እንዳገኙ የገለፁት ሀላፊው የተሰጠን ማብራሪያ ችግሩን በስኬት እንድንፈታ ረድቶናል ብለዋል።
ሀላፊው አክለውም “ ከእግር ኳስ በብዙ ከራቀ ከባቢ እውቀት ቀስመን የተጨዋች ችግር መፍታታችን ልዩ አጋጣሚ ነው "ሲሉ ገልፀውታል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe