አርቴታ ተጨዋቾቻቸውን ምቾት እንደነሱ ገለፁ !

አርቴታ ተጨዋቾቻቸውን ምቾት እንደነሱ ገለፁ !
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በቅድመ ውድድር ወቅት ወጣ ያለ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ሆን ተብሎ ተጨዋቾቹ አስቸጋሪ ጊዜ እንዲያሳልፉ መደረጉን ተናግረዋል።
የበረራ መዘግየት እንዲኖር አድርገናል ያሉት አርቴታ የመልበሻ ቤቱን ሙቀት ጨምረን አስቸጋሪ አድርገንባቸዋል ብለዋል።
በተጨማሪም ሆን ተብሎ የተጨዋቾቹ ምግብ እንዲዘገይባቸው እና እንዲጠብቁ መደረጉን ገልፀዋል።
እንዲሁም የማሳጃ ጠረጴዛዎችን አንስተንባቸው ነገሮችን በተጨዋቾቹ ላይ ከባድ አድርገናል ብለዋል።
ስለ ምክንያታቸው የተጠየቁት ሚኬል አርቴታ “ ሀሳቡ ቀላል ነው ለተጨዋቾቹ የማይመች ከባቢ መፍጠር ነበር "ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም " ተጨዋቾቹ እንደዚህ አስቸጋሪ ነገር ከገጠማቸው እንዴት መላመድ እንዳለባቸው ይማራሉ "ሲሉ አስረድተዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe