ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አገኘች !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አገኘች !
ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አገኘች !

በ ኦሬገን የ አለም አትሌቲክስ ከ 20ዓመት በታች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች።

በሴቶች 3000ሜ ፍፃሜ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዳግም ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።

አትሌት ዮርዳኖስ ፀጋአብ 8:43.65 በሆነ ሰዓት በመግባት ለሀገሯ ሁለተኛውን ወርቅ አስገኝታለች።

አትሌት ዮርዳኖስ ፀጋአብ የግሏን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ ውድድሩን ማሸነፍ ችላለች።

እንዲሁም አትሌት ሽቶ ጉሚ ሁለተኛ ደረጃ ይዛ በማጠናቀቅ የብር ሜዳልያ አሸንፋለች።

በሁለት ርቀት የተካፈለችው አትሌት ሽቶ ጉሚ በውድድሩ ሁለተኛ የብር ሜዳልያዋን አሳክታለች።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በሜዳልያ ሰንጠረዡ በ 2️⃣ ወርቅ ፣ 3️⃣ ብር እና 1️⃣ ነሀስ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

የሜዳልያ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

1ኛ. አሜሪካ 🥇(6)🥈(5) 🥉🥉
2ኛ. ኢትዮጵያ 🥇🥇🥈🥈🥈🥉
3ኛ. ቻይና 🥇🥇🥈🥉🥉
4ኛ. ኬንያ 🥇🥇🥈🥉🥉
5ኛ. ጣልያን 🥇🥇🥉🥉

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች