ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ የአፍሪካ ቁጥር አንድ መሆን አለመሆን ለእኛ ለውጥ አያመጣም ” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ የአፍሪካ ቁጥር አንድ መሆን አለመሆን ለእኛ ለውጥ አያመጣም ” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ
“ የአፍሪካ ቁጥር አንድ መሆን አለመሆን ለእኛ ለውጥ አያመጣም ” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

“ ዘጠና ደቂቃ ይወስናል ”

የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የነገው የተጋጣሚያቸው ማንነት ለውጥ እንደማያመጣ ተናግረዋል።

“ በሜዳችን ነው የምንጫወተው ነጥቡ ያስፈልገናል ፣ ወደኋላ አንመለስም ” ሲሉ ነው አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የተናገሩት።

“ የአፍሪካ ቁጥር አንድ መሆን አለመሆን ለእኛ ለውጥ አያመጣም ” ያሉት አሰልጣኙ “ ሜዳ ውስጥ እስከገባን ድረስ እንጫወታለን ” ብለዋል።

“ እኛ የምንለው ዘጠና ደቂቃ ይወስናል ነው ” የሚሉት ዮሐንስ ሳህሌ “ ይሄ እግርኳስ ነው ሌሎች ሲሸነፉ አይተናል "ብለዋል።

“ በሜዳችን በህዝባችን ፊት ነው የምንጫወተው ይሄ ለእኛ በጥሩ መልኩ የሚነሳ ነገር ነው ” ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።

“ በልጆቹ በኩል ለመጫወት 100% ዝግጁ ናቸው ሜዳ ላይ ያላቸውን ለመስጠት ዝግጁ ናቸው ” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች