ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ጀማል ሙሲያላ ምን ገጠመው ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ጀማል ሙሲያላ ምን ገጠመው ?
ጀማል ሙሲያላ ምን ገጠመው ?

ጀርመናዊው የባየር ሙኒክ ተጨዋች ጀማል ሙሲያላ ከቀናት በፊት ሜዳ ውስጥ ራሱን መቆጣጠር ተስኖት ወድቆ ነበር።

ጀማል ሙሲያላ በሶስት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በዛሬው ዕለትም ተመሳሳይ ችግር ገጥሞታል።

ሙሲያላ ዛሬ ተቀይሮ ገብቶ የነበረ ቢሆንም ሜዳ ውስጥ ከዘጠኝ ደቂቃዎች በላይ መቆየት አልቻለም።

ሙሲያላ አሁን ላይ በማህበራዊ ትስስር ገፁ በሰጠው ማብራሪያ “ ከምንም በላይ አሁን ሰላም ነኝ “ ብሏል።

ለደረሰው የድጋፍ መልዕክት ያመሰገነው ሙሲያላ “ ጊዜያዊ የጤና እክል ገጥሞኛል “ ሲል አሳውቋል።

ስለ ህመሙ ማብራሪያ የሰጠው ሙሲያላ “ ጊዚያዊ ንቃተህሊናን የማጣት ህመም ነው ነገርግን በቀላሉ መታከም ይችላል “ ብሏል።

አክሎም “ መጀመሪያ ላይ ሲታይ አስፈሪ እንደሚመስል አውቃለሁ ነገርግን አሁን የእኔ የእለት ተዕለት ህይወቴ አካል ሆኗል "ሲል ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች